እርስዎ እና ቤተሰብዎ የእኛ የ MCPS ቤተሰብ አካል በመሆናችሁ በጣም ደስተኞች ነን::
ለ MCPS ወይም ለማህበረሰቡ አዲስ ሊሆኑ ይችላሉ:: ወይም ለብዙ ዓመታት የእኛ የ MCPS ቤተሰብ አካል ሊሆኑ ይችላሉ:: ያም ሆነ ይህ ይንን ድረ-ገፅ ጠቃሚ ሆኖ የሚያገኙት ይመስለኛል:: እኛ ይህንን ያዘጋጀነው ለእርስዎ ነው:: ትምህርት ቤቶች እንዴት እንደሚሠሩ ለማወቅና ከ MCPS ወቅታዊ ዘገባዎች ጋር የሚያገናኝ እንዲሁም አብዛኛውን ጊዜ ጥቅም ላይ የሚውሉ ሠነዶችና አንዳንድ ቪዲዮዎች የሚገኙበት በይነመረብ ነው:: ይህ ሁሉ የሚቀርብልዎትበሚፈልጉት ቋንቋ ነው!
የእርስዎ ልጆች በትምህርት ቤቶቻችን በጣም ጥሩ ትምህርት እንዲያገኙ ለማስቻል እያንዳንዱ ሠራተኛ በትጋት ይሠራል::
ስለዚህ ዳግም ወደ MCPS እንኳን ደህና መጡ!
እዚህ በመሆንዎ ደስተኞች ነን!
ህገወጥ ፈንታንይል/fentanyl በወጣቶች ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ በጋራ መስራት እና ችግሩን በተለያዩ ደረጃዎች ልንቀርፈው ይገባል።የምናዘጋጃቸው ዲስትሪክት አቀፍ መድረኮች ለተማሪዎቻችን፣ ለሰራተኞቻችን እና ለቤተሰቦቻችን እውቀትን እና የመረጃ ሪሶርሶችን የሚሰጡ ከመሆኑም በላይ ንቁ ውይይት ለማድረግ እድሎችን ይፈጥራሉ። ተማሪዎች፣ ወላጆች/ተንከባካቢዎች፣ ሰራተኞች፣እና የት/ቤት መሪዎች የጤና እና የደህንነት እርምጃዎች ለህብረተሰባችን በጣም አስፈላጊ እንደሆኑ እና እንዴት በጋራ መተግበር እንዳለባቸው ለመረዳት አብረው እየሰሩ ናቸው።
ተማሪዎች እስከ ሦስት ቀሪዎችን በዜግነት እንቅስቃሴዎች ላይ ሲሳተፉ በምክንያት እንደቀሩእንዲቆጠርላቸው የማሻሻያ ሃሳብ በቀረበበት ፖሊሲ/Policy KEA ላይ የትምህርት ቦርድየእርስዎን አስተያየ ለመስማት ይፈልጋል።
አስፈላጊ ሰነዶችአማርኛ
MCPSን ይጠይቁ (እንግሊዝኛና ስፓኒሽኛ)
301-309-MCPS(6277)
ሰኞ-አርብ
7:30 -5:30